አሁን በሀገራችን እየታዩ ያሉ ችግሮች ህገ መንግስት ካለማክበርና የህግ የበላይናትን ካለማረጋገጥ የሚነሱ ችግሮች መሆናቸውን ዶ/ር ደብረፅዮን ገልፀዋል

አሁን በሀገራችን እየታዩ ያሉ ችግሮች ህገ መንግስት ካለማክበርና የህግ የበላይናትን ካለማረጋገጥ የሚነሱ ችግሮች መሆናቸውን ዶ/ር ደብረፅዮን ገልፀዋል

የትግራይ ክልል መንግስት ም/ር/መስተዳደር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል በትግራይ ክልል መቐለ ከተማ “ህገ መንግስትና ህብረ ብሄራዊ ፌደራላዊ ስርዓትን ማዳን ለዴሞክራስያዊ ሀገራዊ ኣንድነት” በሚል መሪ ቃል በመካሄድ ላይ በሚገኘው አገር አቀፍ የጋራ የውይይት መድረክ ላይ ተገኝቶው መልእክት ኣስተላልፈዋል፡፡

“የብሄር ግጭቶች መከሰታቸውና በማንነት ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶች መበራከታቸው እንደዚሁም በዜጎች ሂወት ላይ ስጋት እየጨመረ የመጣው በፌዴራል ስርዓት በመመራታችን ሳይሆን ህግን ማስከበር ባለመቻላችን ፣ ህገ መንግስቱ በግላጭ እየተጣሰ የሚያስተካክል ዓቅም በመጥፋቱ ዋነኛው ምክንያት እንደሆነ ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል በመድረኩ ላይ ተገኝቶው ባስተላለፉት መልእክታቸው አስረድተዋል፡፡

ዶ/ር ደብረፅዮን እንደሉት ካለፉት ጥቂት ዓመታት ወድህ በሀገራችን አንጃብቦ የሚታየው ፖለቲካዊ አለመረጋጋት ችግር ምክንያት በህገ መንግስቱ የተረጋገጡ የዜጎች መብቶች በአደባባይና መስፋት እየተጣሱ ይሚታይበት፣ የማንም ብሄር ተወላጅ ተንቀሳቅሶ ለመስራትና ሃብት ለማፍራት የተቸገረበት፣ ከዛም አልፎ ለጥቃት የተጋለጠበት ፣ የህግ የበላይነት የተናደበት ወቅት ላይ እንገኛለን ብለዋል።

ዶ/ር ደብረፅዮን አክሎ አገራችን ኢትዮጵያ በፈጣን እድገትዋ ተጠቃሽ የነበረች ሃገር አሁን ግን ዜጎች በማፈናቀል በዓለም ታዋቂ ወደ መሆን ተሸጋግራለች ካሉት በኃላ፤ እየታየ ያለ ከፍተኛ ስጋት ሁላችን ተባብረን በመታገል ህዝቦቻችን የሚፈልጉት ሰላም፣ ልማትና ዴሞክራሲ ለማስፋት ሰላማችን እያወኩ የሚገኙ ወገኖችን በብቃት መታገል አለብን በማለት መልእክታቸው ኣስተላልፈዋል።

አሁን በሀገራችን እየታዩ ያሉ ችግሮች ህገ መንግስት ካለማክበርና የህግ የበላይናትን ካለማረጋገጥ የሚነሱ ችግሮች መሆናቸውን ዶ/ር ደብረፅዮን ጠቁሞዋል፡፡

ዶ/ር ደብረፅዮን ሀገሪቱ ስርዓት አልበኝነት ነግሶባት መንግስት የሌላት ሃገር እስክ ትመስል ድረስ ዜጎች በማንነታቸው ምክንያት መፈናፈኛ አጥተው በውጥንቅጥ ሁኔታ ውሽጥ በተዘፈቅንበት ባሁኑ ወቅት ጣታቸውን ወደ ፌዴራላዊ ስርዓት የሚቀስሩ አልጠፉም ብለዋል።

የትግራይ መንግስት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *