ህገ- መንግስቱ ሀገሪቱን ከ ዲክታተርሺፕ ወደ ዴሞክራታይዜሽን ያሸጋገረ እንደነበር ተገለፀ

ህገ- መንግስቱ ሀገሪቱን ከ ዲክታተርሺፕ ወደ ዴሞክራታይዜሽን ያሸጋገረ እንደነበር ተገለፀ።

ህገ_መንግስትና ህብረ ብሄራዊ ፌደራልላዊ ስርአቱን የማዳን ሃገር አቀፍ የምምክር መድረክ ዛሬም ከሰዓት በፊት በዶክተር መንበረ ጸሃይ ታደሰ በቀረበው ሃሳብ ህገመንግስቱ የ ለጂትሜሲ ችግር ያልነበረበት፣ ከብዙ ዉይይት እና ክርክር በኃላ የጸደቀ፣ ሀገሪቱን ከ ዲክታተርሺፕ ወደ ዴሞክራታይዜሽን ያሸጋገረ እንደነበር ገልፀዋል።

አክለዉም ህገመንግስቱ በተናጠል ሳይሆን በብሄርነቱ የህግ እዕውቅና የሰጠ መሆኑ፣ራስን በራስ የማስተዳደር መብት የሰጠ፣በማንነት ላይ የተመሰረተ ፌደራሊዝመ እንደሆነ፣ ስልጣን የብሄሮች ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች እንደሆነ ፣የበላይ እና የበታች የሚባል የሌለው እንደሆነ ታሳቢ አድርጎ የተመሰረተ ህገመንግስት እንደሆነ አስረድተዋል።

በህገ_መንግስቱ ዙርያም ፍትሃዊ የሃብትና የልማት ክፍፍል እንዲኖር፣ ማንም ሰው ከህግ በታች እንደሆነ፣ዴሞክራሲን መለማመድ የፈቀደ መሆኑን ገልጠዋል።

ይሁን እንጂ ህገ መንግስት እያለ ግን ደግሞ የሙስናና ብልሹ አሰራር ተግዳሮቶቹ እንደሆኑ አስረድተው፤በችግሮች እና በምፍትሄዎቻቸው መጀመርያ የጋራ መግባባትን መፍጠር፣ህገመንግስቱ ራሱን ወደመከላከል መሸጋገር እንዳለበት፣የህዝቦች ጥያቄ መመለስ የሚቻለውም በምርጫ ስለሆነ ዘግይቶም ቢሆን ምርጫ እንዲካሄድ እና ህገመንግስቱን እና ህብረ ብሄራዊ ፌደራላዊ ስርዓቱን ለማዳን መታገል እንደሚያስፈልግ ዶክተር መንበረ ፀሃይ የገለጡት።

የከሰዓት በኅላ ፕሮግራሙ የቀጠለ ሲሆን፣ ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስም እንደ አንድ ያገባኛል የሚል ዜጋ የራሱን ዳሰሳ አስቀምጧል።በአሁኑ ሰዐት ዶር.ኣብይ ስልጣን ከተረከቡ በኅላ የሃገረ መንግስት ጥንካሬ መዛል፣የህግ የበላይነት አለመከበር፣ተጠያቂነትም መጥፋት ተክስቷል ብሏል።

በየሳምንቱ ሰው ሳይሞት አልፎ አያውቅም፣60% የሃገሪቱ ክፍል ኮማንድ ፖስት ስር ወድቋል፣ከ ሃያ አምስት ዓመታት በኃላ የታጠቀ ተቃዋሚ ፓርቲ መንግስትን መፋለም ችሏል፣ከ 28 ሚልዮን ህዝብ በላይ ላስቸኳይ ግዜ እርዳታ ተጋልጧል፣ ማክሮ ኢኮኖሚውም ወድቋል ብሏል። ዉይይቱ አሁንም እየቀጠለ ይገኛል።​

የትግራይ ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ
ህዳር 24 2012 ዓ/ም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *