የሶስተኛ ወገን ልክፍት “ፊየል ወዲህ ቅዝምዝም ወድያ” ከመሆን የዘለለ ትርጉም የለውም

የሶስተኛ ወገን ልክፍት “ፊየል ወዲህ ቅዝምዝም ወድያ” ከመሆን የዘለለ ትርጉም የለውም፡፡
=====================================

ሰሙኑ አመኒስቲ ኢንተርናሽናል የተባለው የሰብኣዊ መብት ተሟጓች ድርጅት፣ በአማራና በኦሮምያ ክልሎች፣ በፊደራል እና በክልሎች የአመራር አካላት እና የፀጥታ ሃይሎች የደረሰውን ጭካኔ የተሞላበት የሰብኣዊ መብት ጥሰት፣ ግድያ፣ እንግልት፣ ግርፋት፣ እስራት፣ መጎሳቆል፣ መፈናቀል ወዘተ አስመልክቶ፣ ይፋ ያደረገውን ሪፖርት፣ ተንተርሰው የሁለት ክልሎች ማለትም የኦሮምያና የአማራ ክልል አንዳንድ ከፈተኛ አመራሮች፣ እንደተለመደው፣ ከግንቦት 23/2012 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ግንቦት 28/2012 ዓ/ም ባሉት ቀናት ፀሓይ የሞቆውን እውነታ፣ አይናቸውን በጨርቅ ሸፍኖው፣ በክህደት በማድበስበስ፣ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች በተለይም የግፉ ሰለባ በሆኑት ንፁሃን ወገኖች ደጋግመው የሚያሳዩትን ንቀትና ቧልት አሁኑም አስነዋሪ የማን አለብኝነት ባህሪያቸው በአደባባይ የፈፀሙት ግፍ የሚሸፍንላቸው እየመሰላቸው ነጋጠባ የሶስተኛ ወገን ልክፍታቸዉ ህወሓትና የትግራይ ህዝብ ላይ ጣታቸዉ ቀስረዋል፡፡

ይኸውም ህወሓት የቅማንት ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ አስታጥቀዋል፣ የታጠቀ ሓይሉ ምዕራብ ኦሮሚያ ከሚንቀሳቀሰውን ኦነግ-ሸኔ ጋር ወግኖ ተዋግቷል፣ በማለት ያለምንም ይሉኝታ በሚድያ ለፍፏል፡፡ ነገር ግን በኢፌድሪ ሕገ-መንግስት፣ ማንኛውም በሰላማዊና ሕጋዊ መንገድ የሚታገል የፖለቲካ ፓርቲ ሰራዊት ሊኖረው አይችልም፡፡ ህወሓትም እንደ የፖለቲካ ፓርቲነቱ ያስታጠቀው ሰራዊት እንደሌለው የአደባባይ ሚስጥር ነው፡፡ ምናልባት ስልጣን የተቆጣጠረው አካል፣ ከኢፌድሪ የመከላከያ እና የጸጥታ አካላት ውጪ፣ የአገሪቱን ሃብት ያለምንም ከልካይ እንዳሻው እያደረገው ያለው ቡዱን በማን አለብኘነት አሰልጥኖ ያሰማራው የራሱ ሰራዊት ካለው ለኢትዮጵያ ህዝብ ይፋ ያድርግ፡፡ ካልሆነ የተለመደው የሰሞኑ ህወሓት አስታጠቀ ጦር ላከ ወዘተ ትርክት “ከብት ባልዋለበት ኩበት ለቀማ” የሚባለው አባባል ከመድገማቸው፣ የተለመደ ቅጥፈት የተሞላበት ውንጀላቸው፣ ውርደትና ሃፍረት ከመከናነባቸዉ ውጪ በእነሱ የሚደናገር ህዝብ ይኖራል ብሎ፣ ማንም በንፁህ ህልና የሚያስብ የሰው ልጅ ይገምታል ተብሎ አይታሰብም።

ሰለሆነም በትግራይ ህዝብና መንግስት ላይ ያነጣጠረ ብሄር ተኮር ጥቃት እንዲደረግ ሓሰተኛ የበሬ ወለደ ወሬዎች የማሰራጨቱ አባዜ እንዲቆም የትግራይ መንግስትና ህዝብ በጥብቅ ያሳስባሉ ፡፡

የትግራይ የመንግስት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ
መቐለ፡ ግንቦት 29/2012 ዓ/ም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *