ከትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የተሰጠ መግለጫ
====================================
በንፁሃን ደም የጨቀየዉ ፋሽሽታዊ፣ የቁራ ጭሆት፤ ከሃዲው ኣሃዳዊ አምባገነን ቡድን፣ ጀምበሯ እየጠለቀችበት መሆኑን የሚያሳይ ነዉ!!

የሕገ-ወጡ፣ አሃዳዊ አምባገነን ቡድን ፋሽሽት መሪ፣ ትላንት ጥቅምት 27/2013 ዓ.ም በቴሌቪዥን መስኮት ብቅ ብሎ፣ የባጡን የቆጡን ሲዘላብድ አምሽቷል። የትላንቱ የያዙኝ ልቀቁኝ የአብይ አህመድ ዲስኩር፣ አሃዳዊ አምባገነን ቡድኑ፣ አሸባሪና ፋሽሽት መሆኑ ራሱ በግልፅ ያመነበት ነው።

ነገር ግና ፋሽሽት አሃዳዊ አምባገነን ቡድን፣ የትላንቱ ምሽት ከንቱ ቀረርቶ፣ የኢትዮዽያ ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦችን እያባላና፣ ንፁህ ደማቸውን እንደዥረት እያፈሰሰ፣ የስልጣን ኮርቻውን ለማጠናከር የዘየደው እኩይ ተግባር፣ በየቀኑ እየከሸፈበት፣ መንበረ ስልጣኑም በመነቃነቁ የሚይዘውና የሚጨብጠው በማጣቱ፣ የቀን ቅዠት እርቲ ቡርቲ ቧልት መናዘዙ፣ ቡዱኑ ወደ ከርሰ መቃብሩ እያዘገመ መሆኑን በተጨባጭ የሚያሳይ ነው።

መንበረ ስልጣኑን ለመጠጋገን እንዲሁም በሁሉም የሃገሪቱ አካባቢዎች የተነሳበት ትግል አቅጣጫው ለማስቀየስ ሲል፣ ሰሞኑ የትግራይ ብሄር ተወላጆች ብቻ በመሆናቸው ከለጋ እድሜያቸው ጀምሮ ሃገራቸውንና ህዝባቸውን በቅንነትና ታማንኝነት ያገለገሉትን፣ የመከላከያ ሰራዊትና የፌደራል ፖሊስ አባላትና አዛዞች የነበሩት ከያሉበት ተለቅመው አለሃጢያታቸው ግማሾቹ እስር ቤት ታጉረዋል። የቀሩት ደግሞ ከቤት እንዳይወጡ ቁም እስረኛ ሆኗል፤ የተቀሩት ከስራ ተባሯል።

ፋሽሽቱ አሃዳዊ ቡድን የሰራዊት አባላትና ኣዛዦች በነበሩት የትግራይ ተወላጆች፣ የሰነዘረው ዱላ፣ በሁሉም የኢትዮዽያ ኣከባቢ በሰላም ይኖሩ የነበሩት፣ የትግራይ ተወላጆች ባለሃብቶችና ሲቪል ሰርቫንትም፣ የሽብር ተግባሩ ሰለባ ሆናል። ይኸውም በኣዲስ ኣበባ፣ ጋምቤላ፣ ቤኒሻንጉል ጉምዝ፣ እና በሌሎችም ያሉት ባለሃብቶች እየተለቀሙ በመታሰር ላይ ናቸው። ለዓመታት ያፈሩት ሃብት፣ ንብረትና ገንዘብም በመዝረፍ ላይ ነው። ሌላው ቀርቶ አረመንያዊ ኣሃዳዊ አምባገነን ቡድን ወደ ተለያዩ የውጭ ሃገራት፣ በተለይም ወደ መካከለኛው ምስራቅ ይጓዙ የነበሩት የትግራይ ተወላጆች ትላንት ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ጣብያ አግቶኣቸዋል።

ይህ ቡድን በትግራይ ህዝብ ላይ የቦምብ ናዳ ባወረደበት ማግስት፣ ያለምንም ይሉኝታና ማን ኣለብኝነት አሁንም ባወጅኩት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅና ባቋቋምኩት ኮማንድ ፖስት በተለያዩ ከተሞች በሚኖረው የትግራይ ህዝብ ላይ በጦር ውግያ ጀት አውሮፕላን ከሰማይ ቦምብ እያዘነብኩኝ እቀጠቅጣለሁኝ፣ እፈጃችሃለሁኝ ብሎ በግላጭ የትግራይ ህዝብን ደም ለማፍሰስ ወደ ኋላ እንደማይል፣ ፈፅሞ አይችልም እንጂ እንደ ህዝብም ከምድረ ገፅ ለማጥፋት ማንኛውም የጥፋት እርምጃ እንደሚወስድ ዝቷል።

ታድያ ይህ በንፁሃን ደም የጨቀየዉ ፋሽሽታዊ አሃዳዊ ቡድን በምን ስሌትና እሳቤ ነው በኣጠቃላይ ስለ የኢትዮዽያ ብሄር፣ብሄረሰብና ህዝቦች፣ በተለይም የትግራይ ህዝብ ጉዳይ ሊናገር የሚችለው?! ምላሹ ኣጭርና ግልፅ ነው፤ይህ አረመንያዊ ቡድን፣ ኢትዮዽያና ህዝቧ ወክሎ የመናገር ስብእናና ሞራል ፈፅሞ የለውም። ሊኖረውም ከቶውንም ሊታሰብ ቀርቶ ሊታለም አይችልም።

ውጪት ሰባሪው የፋሽሽቱ አሃዳዊ አምባገነን ቡድን መሪ፣ የትግራይ ህዝብና መንግስትን፣ ጨፍልቆ፣ ሲዳማ፣ ሱማሌ፣ ጋምቤላ፣ ቤንሻልጉል ጉምዝ፣ አማራ፣ ኣፋር፣ የደቡብ ኢትዮዽያ ህዝቦች ፣ ኦሮምያ፣ ሐረሪ፣ ኣ/አበባና ድሬዳዋ ላይ እንዳደረገው የራሱን ምስለኔዎች የማስቀመጥ አጉል ህልም እንዳለው ሲዘላብድ አምሽቷል። በዛሬው እለትም በእሱ ሳንባ የሚተነፍሰው እና፣ የፈረሰው የፌደሬሽን ም/ቤት ስብሰባ፣ በትግራይ ጊዝያዊ መንግስት ለማቛቛም ወስነናል የሚል ባልት አስነግረዋል።

ነገር ግን ይህ የቁም ቅዠት በትግራይ ሊተገበር ቀርቶ ሊታሰብ የማይችል ነው።ታሪክ ራሱ ይደግማል እንደሚባለው፣ ከ29 ዓመታት በፊት ማለትም በአፍሪካ ተወዳዳሪ የለውም ሲባል የነበረውና ህልቀ መሳፍርት የሌለው ዘመናዊ የጦር መሳርያ የታጠቀ፣ 500 ሺ (ግማሽ ሚልዮን) ወታደር የነበረው ፋሽሽታዊ ወታደራዊ ደርግ ከእነ ሶንከፍ፣ ግብአተ መሬቱ የገባውና ስርዓተ ቀብሩ የተፈፀመው በዋነኛነት በትግራይ ህዝብና መሪ ድርጅቱ ተጋድሎ እንደሆነ፣ የፋሽሽቱ አምባገነናዊ ቡድን፣ መሪዎችም አሳምረው ያውቁታል። አሁንም ቢሆን ትግራይ የሚተነኩስ የውጭ ወራሪም ሆነ ፋሽሽቱ አሃዳዊ ቡድን፣ ትግራይ መቀበሪያ ነው እንጂ፣ መፈንጫዉ አትሆንም። ለምን ቢባል ትግራይን በተሳሳተና በአጉል ስሌት ለመድፈር የሚቃጣ ማንኛውም የውስጥም ሆነ የውጭ ጠላት ሃፍረትና ሽንፈት የማከናነብ ባህልና እሴት ያለው የትግራይ ህዝብ፣ አሁን ከኣብራኩ የወጣው አዲሱ ትውልድም የአያቶቹና የወላጆቹ አኩሪ የአይበገሬነት ወኔ ተላብሶ ባለፉት ሁለት ተኩል ዓመታት በትግራይ ህዝብ ላይ ሲደርስ የነበረውን ዘርፈ ብዙ ብሄር ተኮር ጥቃት መክቷል። አሁንም በመመከት ላይ ነው። የማታ ማታም ድሉ የራሱ እንደሆነ ፈፅሞ አያጠራጥርም። በኣጭሩ በፈለገው ጊዜና ቦታ፣ የሚፈልገው እርምጃ የመውሰድ ብቃትና ችሎታ ያለው፣ የአላማ ፅናት የተለበሰው የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሚመራው የትግራይ ህዝብ አዲስ ተጨማሪ ደማቅ ታሪክ እንደሚፅፍ፣ በአጠቃላይ ወዳጅም ጠላትም፣ በዋነኛነት የኢትዮዽያ ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ፈፅሞ ሃሳብ ሊገባቸው እንደማይገባ ሊሰመርበት ይገባል። ምክንያቱም የሽብር ጋጋታና ቀረርቶ ቀረቶ ሰማይና መሬት ቢገላበጥ የትግራይ ህዝብ ማንነቱን አሳልፎ ለማንም ምድራዊ ሃይል እንደማይሰጥ በተግባር ያስመሰከረ ህዝብ ስለሆነ ነው።

የኢትዮዽያና የኤርትራ ህዝቦች ቀንደኛ ጠላት የሆነው የሻእቢያ መሪ ኢሳያስ አፈወርቂ ማለትም “ኢትዮዽያ መግዛት የሚቻለው በታትነህ ነው። ለኢትዮዽያ የመቶ ዓመት የቤት ስራ እንሰጣታለን፣ ከአማራ ጋር አብሮ መኖር ቀርቶ መለመን አይቻልም።” በማለት ኢትዮጵያን የማፈራረስ እኩይ ተግባሩ እያፋጠነ ያለው፤ ኢሳያስ አፈወርቂ፣ አንጡራ የኢትዮጵያ የጦር መሳሪያና ወታደሮች ያስረከበ ከሀዲው ፋሽሽት አሃዳዊ አምባገነን ቡዱን ቅንጣት ታክል የኢትዮጵያዊነት ስሜት እንደሌለው በገሃድ አሳይታል፡፡

ባጭሩ ፋሽሽቱና አሸባሪው አሃዳዊው አምባገነን ቡድን በትግራይ ህዝብ ያወጀው ጦርነት የትግራይ ህዝብን ብቻ አይጎዳም። ኢትዮጵያን የሚበታትን፣ ስድስት የምስራቅ አፍሪካ ሃገራትን፣ የሚያፈራርስና የአሸባሪዎች መፈንጫ የሚያደርግ አደገኛ የሽብር ጦርነት ነው። ስለዚህ የኢትዮጵያ ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች የራሳችሁን እድል በራሳችሁ ለመወሰን የጀመራችሁት ትግል በተደራጀ አኳኋን አጠናክሯችሁ ልትቀጥሉበት ይገባል፡፡የኢትዮጵያ ሉአላውነት ለማስከበር ዋልታና መከታ የሆንከው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትም ከማንኛውም የኢትዮጵያ ብሄር፣ ብሄረሰብና ህዝብ ጋር ደም ልትቃባ አይገባም። ይልቁንም የሰሜን እዝ አመራሮችና የሰራዊት አባሎች የወሰዱት አቋም እንደምሳሌ ወስደህ ልትተገብር ይገባል፡፡

በመጨረሻም የትግራይ ህዝብና ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት፣ የትላንት፣ የዛሬም ሆነ የነገ ፍላጎትና ምኞት የተፈጠሩ ችግሮች በሰላምና በውይይት ብቻ እንዲፈቱ ነው፡፡ ምንም እንኳን በአሸባሪውና በጦር አምላኪው አሀዳዊ አምባገነን ቡዱን አሻፈረኝ ባይነት የሰላም በር የተዘጋ ቢሆንም እስከ መጨረሻዋ ደቂቃ ጥረቱ ይቀጥላል፡፡ በአሁኑ ወቅት በንፁሀን ደም የጨቀየዉ ፋሽሽታዊ የቁራ ጭሆት እያሰማው ያለው ከሀዲው አሀዳዊ ቡዱን ጀምበሯ እየጠለቀችበት መሆኑን የሚያሳይ ብለዉ የትግራይ ህዝብና መንግስት ያምሉ። ስለዚህ የኢትዮጵያ ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች፣ የኢትዮጵያ ፌዴራሊስት ሃይሎች ጥምረት ያወጡት የሰላም ጥሪ ተግባራዊ እንዲሆኑ፣ ፋሽሽታዊ አምባገነናዊ ቡዱንም፣ ይህ የሰላም አማራጭ ወዶ ሳይሆን ተገዶ እንዲቀበለው እንድታደርጉ በድጋሚ ጥሪያችንን እናቀርባለን። ምክንያቱም በአሁኑ ወቅት ከዚህ የተሻለ የመፍትሔ አማራጭ የለምና ነው!!

የትግራይ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ
28 ጥቅምት/2013 ዓ/ም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *